አዳዲስ ዜናዎች

የቅርብ ጊዜ ልጥፍ

  •     | ሀገራዊ ዜና
  •     | ሀገራዊ ዜና
  •     | ሀገራዊ ዜና
  •     | የጌዴኦ ዞን ዜና
  •     | ክልላዊ ዜና

የጌዴኦ ዞን ዜና



  • የጌደኦ ዞን ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊና አለማቀፋዊ ሁኔታ ያካሄዱት የምክክር መድረክ በመሠረታዊ ሀሳቦች መግባባት በመፍጠር ተጠናቋል። መድረኩን የመሩት የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ(ዶ/ር) አመራሩ መረጃ ተኮር ተግባቦትን ከህብረተሰቡ ጋር በመፍጠርና ጤናማ ማህበራዊ መስተጋብር በመፍጠር በተሳሳቱ መረጃዎች ህብረተሰቡ እንዳይሸበር የማድረግ ድርብ ኃላፊነት አለበት ብለዋል። አያይዘውም የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ስሜት ኮርኳሪ አጀንዳዎችን ወደ ህዝቡ በመርጨት ተግባር የተሰማሪፉ አካላትም መኖራቸውን በውል በመገንዘብ አስፈላጊውን የአጸፋ ሥራ መስራት የአመራሩ ቁልፍ ተግባር እንደሆነም ጠቁመዋል። አሁን ላይ በአለማቀፍ ደረጃ በተለይም በመካከለኛ ምስራቅ፣ አሜሪካና እስራኤል መካከል እየተፈጠረ ያለ ሁኔታ የሚያልፍና ጊዜያዊም ቢሆን መሠረታዊ ጉዳቶችን እያስከተለ ይገኛል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ሀገር-በቀል የሆኑ የአካባቢ ግብርና ሥራዎች በቅርበት በመደገፍ አርሶ አደሩን በማበረታታት እና ሌሎች ተግባራትን በማከናወን ያስፈልጋልም ብለዋል። የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ ኢንጂነር ተመስገን ጥላሁን በበኩላቸው የብልጽግና አመራር እንደመሆናችን ፈተናዎችን ወደ እድል ቀይሮ የመንቀሳቀስ እስትራቴጂ በመከተል የህዝቡን ተጠቃሚነትንና ብሔራዊ ጥቅም መሠረት ያደረገ አማራጮችን በመከተል ወቅታዊውን አለማቀፍ ሁኔታ ማለፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። በመድረኩ የተሳተፉ ከፍተኛ አመራሮችም የወቅቱን ሀገር አቀፍ እና አለምአቀፋዊ ሁኔታ በመገንዘብ፣ ዝግጁ በመሆን የሀገሪቷን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ የመሻገር አቅጣጫዎችን በቁርጠኝነት እንደሚተገብሩ ገልጸዋል።

    April 22, 2026

  •     April 22, 2026

  •     April 22, 2026

  •     April 22, 2026

  •     April 16, 2026

  • ተጨማሪ ዜና...

ክልላዊ ዜና



  • በዲላ ክላስተር የክልል ተቋማት የብልፅግና ፓርቲ ኅብረቶች አመራርና አባላት በወቅታዊ ሀገራዊ፣ ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተዘጋጀ የውይይት መርሃ-ግብር መካሄዱ ተመልክቷል። በዲላ ክላስተር የክልል ተቋማት የብልፅግና ፓርቲ ኅብረቶች አመራርና አባላት በወቅታዊ ፓለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል። ለአመራርና አባላት ውይይት መርሃ-ግብሩ የተዘጋጀ ሰነድ እንዲደመጥ ተደርጓል። በቀረበው ሰነድ ወቅታዊ ሀገራዊ፣ ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ከፖለቲካ፣ ከኢኮኖሚ፣ ከማኅበራዊና ከወታደራዊ እይታዎች አኳያ ለአባሉ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ቁምነገሮች በዝርዝር ተዳስሰዋል። በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ክቡር መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) መድረኩን ባጠቃለሉበት ወቅት ወቅታዊ ሀገራዊ፣ ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን የተገነዘበና የበቃ አመራርና አባል ለመገንባት ስልጠናው መሰጠቱን ገልፀዋል። እስራኤል፣ አሜሪካና ኢራን እያደረጉት ያለው ጦርነት ዓለምን እያናወጠ መሆኑን ክቡር መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) አመልክተው ተለይ የዳበረ ኢኮኖሚ በሌላቸው ሀገራት ዳፋው የበረታ ተፅዕኖ እያደረሰ መሆኑን አብራርተዋል። በበርካታ ተግዳሮቶች ተጠምዳ የቆየች ሀገር የለውጡ መንግሥት መረከቡን ያነሱት ክቡር መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) ዲፕሎማሲያችንን ማጠናከር፣ በብዝሃ-ዘርፍ ኢኮኖሚ ላይ መሥራት፣ ግብርናን በማሻገር የገጠር ትራንስፎርሜሽንን ማረጋገጥ፣ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣ ፈተናን ወደ ዕድል መቀየር፣ የንግድ መስመሮችን ነፃ ማድረግ እንዲሁም ህገወጥ የምርት ዝውውርና ግብይትን መታገል እና የግብርና ኢኒሼቲቮችን መተግበር ከአመራሩና አባሉ ይጠበቃል ብለዋል። የብልፅግና ትልሞችን መከተል የበለፀገችና ተምሳሌት የሆነች ኢትዮጵያን ለመገንባት ያስችላል ያሉት ክቡር መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) አመራሩና አባሉ ቀጣይነት ባለው አቅም ግንባታ ራሱን ማብቃት፣ ውጤታማ ማድረግና ለተልዕኮ ብቁ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል። ከፊት ለፊታችን 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሀገራችን እንደምታካሂድ የጠቆሙት ክቡር መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) የፓርቲያችን አመራርና አባላት ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ተዓማኒ፣ አሳታፊ እና ውጤታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻውን ከመወጣት በተጨማሪ ፓርቲውን በመምረጥ ብልፅግናን ማስቀጠል እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል። በመድረኩ የተሳተፉ የፓርቲው አመራርና አባላት ከቀረበው ቁምነገር ለቀጣይ ተልዕኮ የሚያዘጋጅ ጠቃሚ ግብዓት መጨበጣቸውን ገልፀዋል። አመራርና አባላቱ በቀጣዩ ምርጫ በንቃት በመሳተፍ ለፓርቲው አሸናፊነት በቁርጠኝነት እንረባረባለን ብለዋል። በመድረኩ በዲላ ክላስተር የክልል ተቋማት የኢኮኖሚ ቁጥር አንድ፣ ሁለትና ሦስት የብልፅግና ፓርቲ ኅብረቶች አመራሮችና አባላት መሳተፋቸው ተዘግቧል።

    April 22, 2026

  •     March 4, 2026

  •     February 18, 2026

  •     February 18, 2026

  •     February 18, 2026

  • ተጨማሪ ዜና...

ሀገራዊ ዜና



  • በመላው ዓለም የመጻሕፍትና የደራሲያን የቅጂ መብት ቀን ለ31ኛ ጊዜ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። ቀኑ መጽሐፍን እንደ ንባብ መሣሪያ ብቻ ሳይሆን፣ ማኅበረሰብን የሚቀይርና ሐሳብን ወደ ተግባር የሚተረጉም ታላቅ ኃይል እንዳለው የሚታሰብበት ነው። እ.ኤ.አ. ከ1995 ጀምሮ በዩኔስኮ (UNESCO) አማካኝነት የጸደቀው ይህ ቀን፣ የደራሲያንን መብት ለማስከበር እና ንባብን ለማበረታታት ያለመ ነው። የቀኑ መመረጥም በዓለም ታሪክ ታላላቅ የሚባሉት ደራሲያን (ዊልያም ሼክስፒር እና ሚጌል ደ ሰርቫንቴስ) እ.ኤ.አ. በ1616 በተመሳሳይ ቀን ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ተከትሎ ለደራሲያኑ የሚሰጠውን ክብር ከፍ ለማድረግ ታስቦ ነው። መጽሐፍት በታሪክ ውስጥ የሰው ልጅን ዕውቀት በመሰነድ ረገድ የማይተካ ሚና አላቸው። በዚህ ረገድ ጥቂት እውነታዎችን ስንመለከ ቅዱሳት መጻሕፍት በዓለም ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ቅጂዎች በመሸጥ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ። ዘንድሮ የሞሮኮዋ መዲና ራባት የዓለም የመጽሐፍት መዲና በመሆን ተመርጣለች። ኢትዮጵያም የራሷ ፊደል እና የዳበረ የጽሑፍ ታሪክ ያላት ሀገር እንደመሆኗ፣ በአሁኑ ወቅት የንባብ ባህልን ወደ ልማት የመቀየር ተግባር በስፋት እየተከናወነ ይገኛል። በአዲስ አበባ የሚገኙ እና ለ24 ሰዓታት ክፍት የሆኑ ዘመናዊ ቤተ-መጻሕፍት ንባብን ወደ ዕውቀት በመለወጥ ለወጣቶች ትልቅ ተስፋ ሆነዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ"መደመር" እሳቤ የጻፏቸው መጻሕፍት ንባብን ከሀገር ግንባታ ጋር አስተሳስረዋል። ከእነዚህ መጻሕፍት ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በክልሎች ቤተ-መጻሕፍትን ለመገንባት መዋሉ፣ ንባብ እንዴት ወደ ተጨባጭ ልማት እንደሚቀየር ማሳያም ነው። መጽሐፍት ከትምህርት እና ከመዝናኛነት ባሻገር፣ ትውልድን የሚያቀኑ እና ሀገርን ወደ ብልጽግና የሚያመሩ የሐሳብ ማመንጫዎች መሆናቸውን የዛሬው ቀን ያስገነዝበናል።

    April 23, 2026

  •     April 23, 2026

  •     April 22, 2026

  •     April 22, 2026

  •     April 22, 2026

  • ተጨማሪ ዜና...

ዓለም አቀፍ ዜና



  • በመካከለኛው ምሥራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት ወር በደፈነበት በዚህ ወቅት፣ ቀጣናው በሰላም ተስፋ እና በመሠረተ ልማቶች ላይ ሊፈጸም በሚችል ጥቃት ስጋት ውስጥ ወድቋል፡፡ አሜሪካ ለኢራን ያቀረበችው ባለ 15 ነጥብ የሰላም ዕቅድ እስከ አሁንም ተስፋ ሰጪነቱ እንዳልደበዘዘ እና የድርድር ጥረቶች መቀጠላቸው ተገልጿል፡፡ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ድርድሮቹ በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ በኢራን የኢነርጂ ተቋማት ላይ ሊሰነዘር የነበረውን ጥቃት እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ አራዝመዋል፡፡ ኢራንም በበኩሏ የፓኪስታን የነዳጅ ጫኝ መርከቦች በሆርሙዝ ሰርጥ እንዲያልፉ መፍቀዷ ለዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ እንደ ትልቅ ተስፋ ተወስዷል፡፡ ሆኖም ቴህራን የአሜሪካው ዕቅድ "ልክ ያለፈ ፍላጎት ያረፈበት ነው" በሚል የራሷን አምስት ቅድመ ሁኔታዎች ማቅረቧ፣ የሰላም ሂደቱ በተፈለገው ፍጥነት እንዳይራመድ እክል መሆኑ አልቀረም፡፡ ጦርነቱ ወደ ባሕር ስር የኢንተርኔት መሠረተ ልማቶች ሊሸጋገር ይችላል የሚለው ጉዳይም ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል፡፡ የኢራን አብዮታዊ ዘብ በቀይ ባሕር እና በሆርሙዝ ሰርጥ ስር የሚያልፉ የኢንተርኔት ኬብሎች የጥቃት ዒላማ ሊሆኑ እንደሚችሉ ማስጠንቀቁን ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ ዘግቧል፡፡ እነዚህ ኬብሎች ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነውን የዓለም የኢንተርኔት ግንኙነት እና የባንክ ግብይቶች መተላለፊያ ናቸው፡፡ እንደ ጎግልና ሜታ ያሉ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች መሰል አደጋ ቢከሰት መረጃዎቻቸውን በሌላ አማራጭ አቅጣጫ ለማስተላለፍ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ በአሜሪካ እና ኢራን መካከል የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች ወደ ስምምነት የሚያመሩ ከሆነ ግን ዓለም እፎይታን እንደምታገኝ የቀጣናው የፖለቲካ ተንታኞች እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

    March 29, 2026

  •     March 29, 2026

  •     January 24, 2025

  •     January 23, 2025

  •     January 22, 2025

  • ተጨማሪ ዜና...

ስፖርት



  • በኢትዮጵያ ሊግ 27ተኛ ሳምንት ጨዋታ መርሃግብር ቢሾፍቱ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ይርጋጨፌ ቡና ሀላባ ሸገርን 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል ። ይሁን ገላጋይ እና ሀይላብ በቀለ የማሸነፊያ ግቦች ለይርጋጨፌ ቡና ከመረብ ላይ ማሳረፍ የቻሉ ተጫዋቾች ናቸው ። ከጨዋታው ሙሉ ሦስት ነጥብ ማገኘት የቻለው ይርጋጨፌ ቡና ነጥቡን ወደ ሃምሳ ስድስት ከፍ በማድረግ ወደ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ዳግም ለመመለስ የሚያደርገው ጉዞ አጠናክሯል ። በማሙሽ ኢሳያስ

    March 30, 2026

  •     March 29, 2026

  •     March 29, 2026

  •     March 26, 2026

  •     March 10, 2026

  • ተጨማሪ ዜና...

ቢዝነስ



  • ዲላ ፣ ጥር 12፣ 2017 ጌ.ቲቪ) በያዝነው የበጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ለውጭ ገበያ ከቀረበየቡና ምርት 908 ነጥብ 47 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

    ገቢው የተገኘው ለውጭ ገበያ ከተላከ 204 ሺህ 206 ነጥብ 63 ቶን የቡና ምርት መሆኑን የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የግብይት ዘርፍ ኃላፊ ሻፊ ኡመር ዛሬ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡

    አፈጻጸሙም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ86 ሺህ 251 ነጥብ 17 ቶን ወይም 73 በመቶ ብልጫ አለው ብለዋል፡፡

    እንዲሁም በገቢ ደረጃ የ337 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወይም 59 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ነው በመግለጫቸው ያነሱት፡፡

    በአጠቃላይ በግማሽ ዓመቱ 133 ሺህ 63 ነጥብ 49 ቶን የቡና ምርት በመላክ 714 ነጥብ 99 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

    በበጀት ዓመቱ ከቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ንዑስ ዘርፍ ለማግኘት የታቀደውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ገቢ ለማሳካት ዝርዝር ዓመታዊ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መገባቱንም አመላክተዋል፡፡

    በዕቅዱ ላይም የግብይት ተዋንያኑን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ በስፋት በመሥራት የኤክስፖርት መጠን እንዲያድግ እንዲሁም ምርቶቻቸውን በጥራት ወደ ውጭ መላክ እንዲችሉ መስማማት ላይ በመድረስ የበጀት ዓመቱ ሥራ መጀመሩን አስረድተዋል፡፡

    January 23, 2025

  •     January 22, 2025

  •     August 16, 2021

  •     January 22, 2025

  •     August 16, 2021

  • ተጨማሪ ዜና...

| የአየር ሁኔታ


DILLA, Gedeo Zone, South Ethiopia WEATHER

| የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች


ሳይንስና ቴክኖሎጂ



  • አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እንደ ሰው ለማሰብ እና ለመማር በተዘጋጁ ማሽኖች ውስጥ የሰዎችን የማሰብ ችሎታ ማስመሰልን ያመለክታል። የ AI መስክ የማሽን መማርን፣ የተፈጥሮ ቋንቋን ማቀናበርን፣ ሮቦቲክስን እና የኮምፒውተር እይታን ጨምሮ የተለያዩ ንዑስ መስኮችን ያጠቃልላል።

    የ AI ምርምር ዓላማ እንደ የተፈጥሮ ቋንቋ መረዳት፣ ቅጦችን ማወቅ፣ ችግሮችን መፍታት እና ውሳኔዎችን የመሳሰሉ የሰው ልጅ እውቀትን የሚሹ ተግባራትን ማከናወን የሚችሉ ስርዓቶችን ማዘጋጀት ነው።
    ▎ ታሪካዊ ዳራ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፅንሰ-ሀሳብ ከጥንት ታሪክ የተመለሰ ቢሆንም መደበኛው ጥናት የተጀመረው በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ነው። ቁልፍ ክንውኖች የሚከተሉትን ያካትታሉ:
    • 1950ዎቹ፡- አላን ቱሪንግ የቱሪንግ ፈተናን በማሽን ውስጥ የማሰብ ችሎታ መስፈርት አድርጎ አቀረበ።
    • 1956፡ የዳርትማውዝ ኮንፈረንስ AI እንደ የጥናት መስክ መወለዱን አመልክቷል። • 1960ዎቹ-70ዎቹ፡ እንደ ELIZA እና SHRDLU ያሉ ቀደምት AI ፕሮግራሞች የተፈጥሮ ቋንቋን የማቀናበር ችሎታዎችን አሳይተዋል።
    • 1980ዎቹ፡ በተወሰኑ ጎራዎች ውስጥ የሰውን እውቀት ለመኮረጅ ህግን መሰረት ያደረገ አመክንዮ የተጠቀሙ የባለሙያዎች ስርዓት መጨመር።

    • 1990ዎቹ-2000ዎቹ፡ በማሽን መማር እና በመረጃ መገኘት ላይ የተደረጉ እድገቶች በ AI መተግበሪያዎች ላይ ከፍተኛ እድገት አስገኝተዋል።
    ▎ ዋና ፅንሰ ሀሳቦች በ AI 1. ማሽን መማር (ML): • ስርዓቶች በግልፅ ፕሮግራም ሳይዘጋጁ ከውሂብ እንዲማሩ እና አፈጻጸማቸውን በጊዜ ሂደት እንዲያሻሽሉ የሚያስችል የ AI ንዑስ ስብስብ።

    • የኤምኤል ዓይነቶች፡- • ክትትል የሚደረግበት ትምህርት፡ ሞዴሉ በተሰየመ መረጃ (የግቤት-ውፅዓት ጥንዶች) ላይ የሰለጠነ ነው። • ክትትል የማይደረግበት ትምህርት፡ ሞዴሉ ያልተሰየመ ውሂብ ውስጥ ያሉትን ንድፎችን ይለያል።
    • የማጠናከሪያ ትምህርት፡ ሞዴሉ ከአካባቢ ጋር በመገናኘት እና ግብረ መልስ በመቀበል ይማራል።
    2. ጥልቅ ትምህርት፡- • በመረጃ ውስጥ የተለያዩ የአብስትራክት ደረጃዎችን ለመተንተን የነርቭ ኔትወርኮችን ከብዙ ንብርብሮች (ጥልቅ የነርቭ ኔትወርኮች) ጋር የሚጠቀም ልዩ የማሽን ትምህርት ስብስብ።
    4. የኮምፒውተር እይታ፡- • የማሽኖች ችሎታ የመተርጎም እና ውሳኔዎችን ከአለም በሚታየው የእይታ መረጃ ላይ በመመስረት። የኮምፒውተር እይታ አፕሊኬሽኖች የፊት ለይቶ ማወቂያን፣ ነገርን መለየት እና ራሳቸውን ችለው የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎችን ያካትታሉ።

    5. ሮቦቲክስ፡ • በራስ ገዝ ወይም በከፊል በራስ ገዝ ተግባራትን እንዲያከናውኑ AI ከሮቦቶች ጋር መቀላቀል። ሮቦቲክስ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ፣ ኤሌክትሪካዊ ምህንድስና እና የኮምፒውተር ሳይንስን ያጣምራል።

    ▎ የ AI መተግበሪያዎች AI ሂደቶችን አውቶማቲክ በማድረግ፣ የውሳኔ አሰጣጥን በማሳደግ እና ቅልጥፍናን በማሻሻል በርካታ ኢንዱስትሪዎችን እየለወጠ ነው። አንዳንድ ታዋቂ መተግበሪያዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ:

    • የጤና እንክብካቤ፡ AI ስልተ ቀመሮች በሽታዎችን ለመመርመር፣ የሕክምና ዕቅዶችን ግላዊ ለማድረግ እና የታካሚ ውጤቶችን ለመተንበይ ይረዳሉ።

    January 23, 2025


  •     January 23, 2025

  •     January 23, 2025

  •     January 23, 2025

  •     January 23, 2025

  • ተጨማሪ ዜና...

ጤና



  • የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በርክክቡ ወቅት እንዳሉት የደምና ሕብረ ህዋስ አገልግሎቱ፤ በ2015 ዓ.ም ከአይን ባንክ ጋር ከተዋሃደ እንዲሁም በአዲሱ በጸደቀው የጤና አገልግሎት አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር1362/2017 መሠረት የተልዕኮና የአደረጃጀት ለውጥ በማድረግ፤ የአገልግሎት አድማሱን ይበልጥ በማስፋቱ፤ ተቋሙን በደም፣ በህብረ ህዋስ እና በአካል የማስተላለፍ ህክምናዎች ለማዘመን ስራዎችን እየሠራን እንገኛለን ብለዋል።

    የጤና ሚኒስቴር በሁሉም አቅጣጫ የኢትዮጵያ ደምና ሕብረህዋስ ባንክ አገልግሎትን እየደገፈ እንደሚገኝ እና የዛሬውም ድጋፍ የቀጣይ ድጋፍ አንዱ ማሣያ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፣ ድጋፉ 12 ዓይነት የህክምና መሣሪያዎች ያካተተ እንደሆነና በገንዘብም 128 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት እንደሆነ ጠቁመዋል።

    አንድም እናት በወሊድ ወቅት በደም እጥረት ህይወትዋ እንዳያልፍ፤ በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ አደጋዎች አስተማማኝ እና ቀጣይነት ያለው የደም አቅርቦትን ለማረጋገጥ የህብረተሰቡ የበጎ ፍቃድ የደም ልገሣ ተሣትፎ ወሣኝ እንደሆነ የገለፁት ሚኒስትሯ በግልም ይሁን በማህበር ተደራጀተው ለደም ልገሳው ዘወትር ከፊት ለሚሰለፉ የበጎ ፍቃድ ደም ለጋሾች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

    የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ሕዋስ ባንክ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አሸናፊ ታዘበው በበኩላቸው በደም አቅርቦት ሥርዓት ውስጥ የህክምና መሣሪያዎች ሚናቸው ወሣኝ ቢሆንም በሃገር ውስጥ የማይገኙ፣ በግዢ ሂደትም ውስብስብ የጥራት ጉዳይ የሚታይባቸውና ከፍተኛ ሃብት የፈሰሰባቸው በመሆናቸው፤ መሣሪያዎችን በአግባቡና በጥንቃቄ ተጠቅመን አጠቃላይ የደም ሥርዓታችንን ለማሻሻል ሁሉም በትኩረት ሊሠራ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

    አሁን የተደረገው ድጋፍ የመጀመሪያ ዙር ሲሆን በቀጣይ ፍሪጆች እና ሌሎች የህክምና መሳሪያዎች ግዥ ሂደት ላይ በመሆናቸው ሀገር ውስጥ እንደደረሱ የሚሰራጩ መሆኑን አክለው አገልግሎቱ አጠቃላይ የደምና ህብረ ህዋስ ስርአቱን ለማዘመን የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

    ድጋፎቹን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ያስረከቡ ሲሆን ከክልሎች የመጡ የጤና ቢሮ ሀላፊዎች እና ምክትል ሀላፊዎችም በድጋፉ መደሰታቸውን እና ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

    January 23, 2025


  •     August 16, 2021

  •     August 16, 2021

  •     August 16, 2021

  •     August 16, 2021

  • ተጨማሪ ዜና...

ጌዴኦ በፎቶግራፍ